መለስን ያያችሁ…… ወዲህ በሉን!! አንበል ” ከዚያስ”


Breaking News: ESAT Radio reported the passing of Meles Zenawi

http://ecadforum.com/ethiopianvideo/2012/07/30/esat-radio-reported-the-passing-of-meles-zenawi/

  ሞት እልል ያሰኛል? 

መለስ ድሮም ዘንድሮም እያነጋገሩ ነው። ድሮ በአቋማቸው፣ አሁን ደግሞ አሉ ወይስ የሉም? ለዚህ ነው ” መለስን ያያችሁ ” የሚለው የልጅነት ጨዋታ ትዝ ያለኝ። ድሮ ልጅ እያለን መሃረቤን ያያችሁ እያልን ስንጫወት፣ መሃረብ ይደበቅና መሃረቤን ያያችሁ ይባላል። መሃረቡ የተደበቀበትን የሚያውቁ እያጨበጨቡ አላየንም ይላሉ። አንዴ ሳይሆን ፈላጊው ዞሮ እስኪያገኘው ድረስ መሃረቡን የሚጠቁም የለም። ስለጫወታው እዚህ ላይ ላብቃና ስለ አቶ መለስ ላውራ። አቶ መለስ ” ትንታግ ነች ” የሚሏቸው ቀዳማዊ እመቤት ወይ ሃዘኔን ድረሱኝ፣ አለያም ” አታሟርቱ ” ብለው በዛ በትንታግ አንደበታቸው እንቅጩን ቢናገሩ ምን አለበት? ባል ወይ ሚስት ከሁለት አንዱ ቀድመው መሞታቸው ያለ ፣፡የነበረ፣ ወደፊትም የሚቀጥል ነውና!! ዛሬ ሁሉን ደብቀው ከሁለት ወር በላይ የሚመራንን ሳይነግሩን የሚያኖሩን ልክ እንደተደበቀው መሃረብ ያለበትን እያወቁ እንደሚያጨበጭቡት ህጻናት ይመስላሉ። በራሳቸውና በህዝብ ላይ እየተጫወቱ ናቸው።

ልክ እንደጨዋታው ሁሉ አቶ መለስ ያሉበትን ሁኔታ የሚያውቁት የምናወቀው የለም  እያሉ እስከመቼ ሊከርሙ ነው?  አንድ አገርና ህዝብ ማን እየመራው እንዳለ የማወቅ መብት የለውም? የባድሜ ጉዳይ ትዝ አለኝ። የወንድሞቻችን ህይወት ከተገበረ በሁዋላ ለድርድር የተስማሙት አቶ መለስ  በአቶ ስዩም መስፍን አማካይነት የሄጉ ፍርድ ቤት ባድሜ የኢትዮጵያ አካል መሆኗን አረጋገጠ። ተፈረደልን። በማለት በህግ አንዳሸነፍን ነገሩን። ምስኪኑ የአዲስ አበባ ነዋሪ ለባድመ አቀባበል ለማድረግ መስቀል አደባባይ እንዲተም ተደረገ። አዲስ አበባን በድያለሁ፣ ጸረ ልማት ነበርኩ፣ በማለት ራሳቸውን በቴሌቪዥን ሰድበው ሱዳን አምባሳደር የሆኑት አሊ አብዶ ጎል እንዳስቆጠረ የፕሪሚየር ሊግ አጥቂ አረፋ እየደፈቁ በታናናሽ ካድሬዎች ትከሻ ላይ አቅላቸውን ጥለው ሲፎክሩ ዋሉ። አፍታም  ሳይቆይ ሰነዱ ሲታይ ውሸት ሆኖ ተገኘ። አሁን ድረስ ወንድሞቻችን ድሮ በድል ለጨረሱት ጦርነት ዘበኛ ሆነው በረሃ ውስጥ ይኖራሉ። በረሃ ውስጥ በቀበሮ ጉድጓድ ይቀምላሉ፤

እንግዲህ በዚህና በሌሎች በርካታ ጉዳዮች ህዝብ መንግስትን ማመን ተስኖታልና። ስለ አገሩ  የወጪ አገር ሚዲያ ካልነገረው በስተቀር ያገር ቤት ሚዲያዎችን ማመን ካቆመ ቆይቷል። የመንግስት ሚዲያዎች ብቻ ሳይሆኑ ቅምጥ የሚባሉትም ህዝቡን በበሉት መጠን እያዥጎረጎሩት ህዝብና መንግስት በሚዲያ ሆድና ጀርባ የሆኑበት ደረጃ ተደርሷል። ልወደድ ባይ አንዳንድ ጋዜጠኞች ያልተባሉትን ሳይቀር እየቀባጠሩ ሙያውን አርክሰውታል። እንደሚሰማው ከሆነ ገና ለገና ብለው ጥቁር ልብስ በመግዛት ጺማቸውንም ያሳደጉ አሉ። ወገንተኛነት ያለ ቢሆንም ከመጠን ሲወጣ ያጥወለውላል።

ይህ አደገኛና መመለሻ የሌለው የሚመስለው የመንግስትና የህዝብ አለመደማመጥ፣ ምናልባትም መደማመጥ የሚያስፈልግበት ወሳኝ አጋጣሚ ሲመጣ የሚያስከፍለው ዋጋ የከፋ ሊሆን ይችላል። መነሻዬ የመለሰስ ጉዳይ ነውና ወደዛው ላምራ። መለስ በጠና መታመማቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ አደረኩ ያለን ኢሳት፣ አሁን ደግሞ መሞታቸውን አወጆልናል። ይህንኑ የህልፈት ዜና ተከትሎ በምንጭነት የተጠቀሰው አይ ሲ ጂ ለማስተባበል ሞክሯል። እጥር ባለች መግለጫው አቶ መለስን በተመለከተ ያልኩተት ነገር የለም ብሏል። አለመታም ታላቅ ጉድለት ነውና ግራ የተጋባን አለን።

እንደ ዜና ኢሳት ተቋሙን በቀጥታ አልገለጸም። ተቋሙ ውስጥ ያሉትን ምንጮች ነው የጠቀሰውና የተቋሙ መግለጫ ኢሳትን ሙሉ በሙሉ አስተባበለ ማለት አያስችልም። እንደኔ የዜናው ሙሉ ሃላፊነት ያለው ኢሳት ጋሱ ላይ ነው። በሌላ በኩል ኢሳትን መለስ በህይወት ቆመው ካላስተባበሉት በስተቀር አሁን የየትኛውም ወገን መግለጫም ሆነ መረጃ ባራዳ ቋንቋ ” ጆካ” ነው። በዚህ መሰረት መለስ ህይወታቸው ካለፈ ጨዋታውና ፖለቲካው ስለቀጣዩ እንጂ በሞት መደነስ መሆን ያለበት አይመስለኝም። ምንም ይሁን ምን ሞት የሚሳቅበት አይደለም። ቢልልን አልቅሰን፣ ሰው ሰራሹን ሳይሆን የልባችንን ባንዲራ ዝቅ አድርገን የምንቀብረው በስምምነት ያስቀመጥነው መሪ ቢኖረን መልካም ነበር። የምንወደው፣ የሚወደን፣ የምናምነው፣ የማያጭበረብረን መሪ ቢኖረንና ፈቅደን ብንመራ መታደል ነበር። አስኪ አሁንም ከዚያስ በማለት ይህን እናስብ። በሞት ጮቤ እየረገጥን የምንሰነዝረው ቃልና ፉከራ የልዩነቱንና ያለመተማመኑን የሚያጎላ መርዝ ከመርጨት የዘለለ የሚያመጣው ነገር የለምና እንጠንቀቅ። የስድብ ፖለቲካና በስድብ የተካነ አማራጭ የሚቀበል ያለ አይመስለኝምና ሚዛኑን የጠበቀ የፖለቲካ አመራር ከመቼውም በላይ አስፈላጊ ነው። መለስ ኖሩም አልኖሩም ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ በወጉ ላስተዋለ ” ከዚያስ” የሚል ጥያቄ መሰንዘሩ የሚጠቅመው ይመስለኛል። የኤርትራ መንግስት ዝምታም ሌላው የፖለቲካው ጨዋታ አብይ ክፍል ነውና የበሰለ ፖለቲካና የበሰለ አመራር ከሁሉም ወገን ይጠበቃል። የሃይማኖት ጥያቄዎችም ቢጤኑ መልካም ነው። ሁሉንም ጨዋታ ለመጫወት የመጫወቻ ሜዳ ግድ ነውና !! ማረቤን አያችሁ ህዝብ፣ አላየንም ባለስልጣናት፤ ለማንኛውም ነብስ ይማር ወይም በሸታዎን የውሻ ቁስል ያድርግልዎ አቶ መለስ፤ ለሀላችንም ደግሞ አንድ ጥያቄ ላንሳ ” የመለስ ህይወት ቢያልፍ እንደ ፖለቲካ ድል ይቆጠራል?” ስድብም ቢሆን አስቴአየት ለምትሰጡ ለማስተናገድ ዝግጁ ነኝ። እኔ ግን በሞትና በተስካር ለድል መብቃትን የሚመኝ ትግል ራሱ ሙት ነው።

Ethiopia: Crisis Group denies media reports about PM’s fate

Brussels  |   31 Jul 2012

International Crisis Group has no direct knowledge about the state of health of Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi. Crisis Group has never commented on Mr Zenawi’s health or his fate, and is not in a position to speculate about it. Crisis Group categorically denies any media claims to the contrary.

http://www.crisisgroup.org/en/publication-type/media-releases/2012/africa/ethiopia-crisis-group-denies-media-reports-about-pm-s-fate.aspx