ኢትዮጵያ ኤርትራን መደብደቡዋን አስታወቀች


ኢትዮጵያ ኤርትራን ክፉኛ እንደመታች ይፍ አደረገችMap-Ethiopia-Eritrea-military-clash
– የኤርትራ መልሶ ጥቃት የማድረስ አቅም ተዳክሙዋል ተባለ
– ጥቃቱ ሊቀጥል ይችላል የሚል ማስጠንቀቂያም አለበት
የኤርትራ መንግስት በጾረና ግንባር ጥቃት ለመሰንዘር በመሞከሩ የአጸፋ እርምጃ ተወስዷል – መንግስት

የኤርትራ መንግስት እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ጠዋት በጾረና ግንባር ጥቃት ለመሰንዘር በመሞከሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአጸፋ እርምጃ መውሰዱን የኢፌዴሪ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሰራዊት በወሰደው በዚህ ተመጣጣኝ ዕርምጃም፥ የኤርትራ ጦር ጥቃት የማድረስ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መዳከሙንም ነው የጽህፈት ቤቱ መግለጫ የሚያስረዳው።

የኤርትራ ሰራዊት ያሰበውን በመፈጸም ማምለጥ እንደማይችል ከተወሰደው ተመጣጣኝ እርምጃ ትምህርት እንዳገኘ ይገመታል ሲልም ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አስረድቷል፡፡

መግለጫው የኤርትራ መንግስት በራሱ ህዝብ ላይ የሚያካሂደው አስከፊ ጭቆናና የመብት ጥሰት፥ በሰው ዘር ላይ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን በመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት መጠቀሱ ቀውስ ውስጥ እንደከተተውም ገልጿል።

የትናንት ጠዋቱ የትንኮሳ ሙከራም የኤርትራን ህዝብና ዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለማስቀየር ያሰበው ይሆናል ሲልም ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አመልክቷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በወሰደው ጠንካራ የአጸፋ ምት ለጥቃት የተንቀሳቀሰው ኃይል ሙሉ ለሙሉ መመታቱን የጠቀሰው መግለጫው፥ የመከላከያ ሰራዊት ቀጣይ እርምጃ በኤርትራ መንግስት እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን ጽህፈት ቤቱ በአጽንኦት ገልጿል።

የኤርትራ መንግስት ካለው ባህሪ አንጻር ጉዳዩን ከማባባስ የማይቆጠብ ከሆነም መከላከያ ሰራዊት የሚወስደውን ተመጣጣኝና አስተማሪ ቅጣት እንደሚቀጥልም አስረድቷል።

የኢፌዴሪ መንግስት እንደተለመደው ሁሉ ስለጉዳዩ በየጊዜው ለኢትዮጵያ ህዝብ በቂ መረጃ እንደሚሰጥም ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው ጠቅሷል። ምንጭ /ፋና አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2008

“የህወሃት አገዛዝ ጥቃት ሰነዘራብኝ” ኤርትራ


የግጭቱ ፖለቲካ – ግን ሁለቱ ወገኖች የማይስማሙት ለማን ተበሎ ነው? 

ለበረካታ ጊዚያት የሰላም ንግግር እየተካሄደ እንደሆነ ይነገራል። ስምምነቱ ግን ለምን እንደሚፈርስና እንደሚከሽፋ ይፋ አይወጣም። አንዱ ሌላን በመክሰስ፣ አንዱ ብቸኛ ሰላም ፈላጊ በመሆን ህዝብ ፊት ይቀርባሉ። ህዝብ ከሁሉም ወግን ተጠቃሚ ሲሆን አይታይም። ” ንጻነት” እና ” አብዮታዊ ዲሞክራሲ” የተጠበቀባቸውን ያህል አላራመዱም። ወይ ለይቶለት አሸናፊው ወገን ሊታይ አልቻለም። የሰው ልጆች በበረሃ ጉድጉዋድ ሰርተው ይኖራሉ። ድንበር ይጠብቃሉ!! ግን እስከመቼ?

download (4)

“የህወሃት አገዛዝ ጥቃት ሰነዘራብኝ” ኤርትራ
– ግጭቱ ከድጋፍና ከተቃውሞ ሰልፍ ጋር ተያይዙዋል

የ “ህወሃት አገዛዝ ” ሲል የሚጠራውን መንግስት ጥቃት ሰነዘረብኝ ስትል ኤርትራ ከሰሰች። በጁን 12 ማለትም ትናንት በጾረና ግንባር ያልተጠበቀ ጥቃት እንደተካሄደበት፣ የጥቃቱ ዓላማና ውጢት ግልጽ እንዳልሆነለት በመጠቆም መግለጫ ያወጣው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ፣ የኤርትራ መንግስት ደረሰብኝ ያለውን ጥቃትና ቀጣይ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ተጨማሪ መግለጫ እንደሚያውጣም አመልክቱዋል።
የተለያዩ የትግርኛ ድረ ገጾችንና የስልክ ቃለ ምልልሶችን የተከታተለ እንደገለጸልኝ ከሆነ ጦርነት አልተካሄደም። መተነኩዋኮሱ ያለና የኖረ ነው። በተጠቀሰው ቀን ድንበር ላይ ያሉ ወታደሮች ኩዋስ እየተጫወቱ ሳለ ድንገት ተኩስ በመከፈቱ ከኢትዮጵያ ወገን ምላሽ ተሰጥቱዋል። ያሁኑን ለየት ያደረገው ቶሎ አለመቆሙ ነው።
በሌላ በኩል ግን አሁን በያዝነው ወር 23 እና 24 ጄኔቫ የሚደረግ ኢሳያስን የሚደግፉና የሚቃወሙ ሰልፎችን ተከትሎ የተከሰተ ነው የሚሉ ውገኖችም አሉ። የኢሳያስ አፉወርቂን አስተዳደር በመቃወም የሚካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ የሚደገፉ ድርጊቱ ሃሳብ ማስቀየሪያ እንደሆነ ሲናገሩ፣ ደጋፊዎቹ በበኩላቸው በተቃራኒው “ወያኔ ሆን ብሎ አደርጎታል” ሲሉ ይከራከራሉ። ይህ ሲጻፍ ከኢትዮጵያ ወገን በኦፊሳል የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ብሉምበርግ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩን ጠቀሶ እንዳለው በጁን 8 የተባበሩት መንግስታት ይፋ ያደረገውን ጉዳይ አቅጣቻ ለማስቀየር ነው።
የተባበሩት መንግስታት ኤርትራ ላይ የያዘውንም ይሁን ወደፊት የሚይዘውን አቁዋም ላይ ይህ ግጭት ምንም ዓይነት እንድምታ የለውም በሚል ለጉዳዩ ብዙም ድንታ የሌላቸው ይናገራሉ። ” በድጋፍና በተቃውሞ ሰልፍ መነሻ የሚወሰን ነገር እንደሌለ አበሻ የሚረዳው መቼ ነው? ለራስ እርካታ ካልሆነ በስተቀር ነጮቹ ፍልጎታቸውን ካማሳካትና ለፍላጎታቸው የሚጠቀማቸውን ከማድረግ አይቦዝኑም” ባይ ናቸው።
ዜናውን በማወጅ ቅድሚያ የያዘው አውራ አምባ ታይም ምንጮቹን ጠቀሶ ሰፊ ሽፋን ያለው ጦርነት በጾረናና በዛላምበሳ በኩል እንደተካሄደ፣ ጦርነቱን የጀመረችው ደግሞ ኤርትራ እንደሆነች በ12.06.10 ማስታውቁ የሚታወስ ነው።
ለሁሉም ሰላም ያዋጣል!!

የኤርትራ አጭር መግለጫ

TPLF Regime launches an attack

The TPLF regime has today, Sunday 12 June 2016, unleashed an attack against Eritrea on the Tsorona Central Front. The purpose and ramifications of this attack are not clear. The Government of Eritrea will issue further statements on the unfolding situation.

Ministry of Information

Asmara

12 June 2016

ትናንት የተቋረጠው ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል


– የፈተናው መደገም ኦሮሚያ ላይ ደስታ ፈጥሩዋል

የ፩፪ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰረቁ ከታወቀ በሁዋል የትምህርት ሚኒስቴር ወሬው አሉባልታ መሆኑን ጠቅሶ ፈተናው በተያዘልት ጊዜ መሰረት እንደሚካሄድ አሳውቆ ነበር። አፍታም ሳይቆይ ፈተናው መሰረቁ ይፋ በመታወቁ እንዲቁዋረጥ ትምህርት ሚኒስቴር አዘዘ። ከዚያም አክሎ ከሰኔ ፪፯ ቀን እስከ ፴ ቀን ድረስ ፈተናው በድጋሚ እንደሚካሄድ መወሰኑ ተጠቁሙዋል። የቀኑ መራዘም ያስደሰታቸው የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ደስታ እንደተሰማቸው ተደምጡዋል። ትልቁ ጥያቄ ሰኔ ፪፯ የሚሰጠው ፈተና ተመሳሳይ ችግር እንዳይገጠመው ዋስትና አለመኖሩ ነው። አንዳንድ የማህበራዊ ገጽ መረጃዎች የሰላ ትችት መሰንዘሩን ያመለክታሉ። ለሁሉም ዋልታ ከዚህ በታች ያለውን ዜና በድረ ገጹ አትሙዋል።

ትናንት ተቋርጦ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን የትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አደረገ። የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በተለይም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ከሰኔ 27 ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት ድረስ ፈተናው ይሰጣል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና ኮድ 14 የእንግሊዝኛ ፈተና መውጣቱ በመረጋገጡ እና ሌሎች ፈተናዎች ላለመውጣታቸው ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባለመኖሩ እንዲሰረዝ መደረጉን ትናንት ሚኒስትሩ መግለፃቸው ይታወሳል። አሁን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት እና አሰጣጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጥበቃ የሚከናወን እንደሚሆንም ነው ሚኒስትሩ የገለፁት።

ሀገር አቀፍ ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጥናትና ምርምር ማዕከል አማካኝነት በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚዘጋጅ ያስረዱት አቶ ሽፈራው፥ ባለሙያዎቹ ተፈታኝ የስጋ ዘመድ እንደሌላቸው ተረጋግጦ በፈተና ዝግጅት እንዲሳተፉ እንደሚደረግም ተናግረዋል።

ፈተናው በመቀጠልም በተደራጀ እና ምስጢራዊነቱን በጠበቀ መልኩ የህትመትና የስርጭት ስራው እንደሚከናወንም ነው ያረጋገጡት። በፈተና ስርቆት ተግባሩ ላይ የተሳተፉ አካላትም ህጉ በሚፈቅደው መሰረት አስፈላጊውን ማጣራት በማካሄድ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እንደሚደረግም ሚኒስትሩ ገልፀዋል። አቶ ሽፈራው ተማሪዎች በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለፈተና ዝግጀት በማድረግ በተጠቀሰው ጊዜ ፈተናውን እንዲወስዱ አሳስበዋል።

ግንቦት 23፣ 2008 (ዋኢማ)-

አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መቋረጡን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ


ፈተናው መሰረቁን በማጋለጥ ቅድሚያ የያዙትን ግለሰቦች ወይም አካላት መሸለም ይገባል!!

በ800 የፈታና ጣቢያዎች ዛሬ ሊሰጥ የነበረው አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መቋረጡንና ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ትshiferawምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ ።
ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በአገሪቱ 800 የፈተና ጣቢያዎች መካከል በአንዱ ጣቢያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና ተሰርቆ በማህበራዊ ድህረገጽ በመውጣቱ ፈተናው እንዲቋረጥ ተወስኗል።
ወጥቶ የተገኘው የፈተና ወረቀት ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የታተመ መሆኑ በመረጋገጡ ከግንቦት 22 እስከ 25/2008 ዓመ
ተ ምህረት ሊሰጥ የነበረው ፈተና መቋረጡን ሚኒስትሩ አመልክተዋል።
በማያያዝም ትምህርት ሚነስቴር ለፈተና ተዘጋጅተው የነበሩ ተማሪዎችንና ወላጆችን ይቅርታ ጠይቋል።
ሚኒስትሩ አያይዘውም ፈተናው የተሰረዘባቸው ተማሪዎች በቅርብ ሌላ ፈተና እንደሚሰጣቸው አስታውቀው ጉዳዩን በሚመለከት ተከታታይ መግለጫ ለተማሪዎቹ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
ፈተናው እንዲወጣ ባደረጉ ግለሰቦች ክትትልና ምርመራ በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አቶ ሺፈራው አስታውቀዋል ።
ከዚህ በፊት እንደዚህ ዓይነት ችግር አጋጥሞ አያውቅም ያሉት ሚኒስትሩ ህዝቡ የራሱና የልጆቹን ድካምና ልፋት እንዲሁም የሞራል ውድቀት ያስከተሉ አካላት ላይ በሚወሰድ እርምጃ ከመንግስት ጎን እንዲቆም ጥሪ አስተላልፈዋል ።
አቶ ሺፈራው አያይዘውም በቅርቡ ከ10 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የተሰጠው ፈተና ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ ፈተናው ታሪሞ ሲጠናቀቅ በተለመደው ጊዜ ውጤቱ ለተማሪዎች እንደሚሰጥም አስታውቀዋል ። ምንጭ ግንቦት 22/2008(ዋኢማ) –
ፎቶ የራሴ ነው

‹‹ሕገ መንግሥቱ በሰጠኝ መብትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባረጋገጡት ድርጊት ልከሰስ አይገባም››


የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሕገ መንግሥቱ በሰጠኝ መብትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባረጋገጡት ድርጊት ልከሰስ አይገባም አሉ ።በፌስቡክ አድራሻቸው አመፁና ብጥብጥ ቀስቃሽ ጽሑፎችን በማሠራጨት፣ የኦነግን ዓላማ ለማስፈጸም ተንቀሳቅሰዋል ተብለው በሽብር ተግባር ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ የቀረበባቸውን ክስ ተቃወሙ፡፡ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ ‹‹ሕገ መንግሥቱ በሰጠኝ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትና በክሱ የተጠቀሰው ብጥብጥና አመፅ የመልካም አስተዳደር ዕጦት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባረጋገጡበት ሁኔታ ልከሰስ አይገባም፤›› ሲሉም ተቃውሞአቸውን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡yonatan

በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ የነበረው ብጥብጥና አመፅ ‹‹የመልካም አስተዳደር ዕጦት ችግር ነው፡፡ የሌላ ሦስተኛ አካል ተሳትፎ የለበትም፤›› በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ማረጋገጣቸውን ያስረዱት ተከሳሹ አቶ ዮናታን፣ የተለያዩ የፌደራልና የክልል ሥራ ኃላፊዎችና ባለሥልጣናትም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር በማጠናከር፣ ዕርምጃ የወሰዱበትና በርካታ ሹማምንትም ከኃላፊነት መነሳታቸውን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የሚያውቀውና ከማንም ያልተደበቀ በመሆኑ፣ ግልጽ የሆነ የሕግ ግምት (Judicial Notice) የሚወስድበት ጉዳይ መሆኑን አቶ ዮናታን አክለዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች የተደረገው አመፅና ብጥብጥ የመልካም አስተዳደር ዕጦት መሆኑ ተረጋግጦ ሳለ፣ በቀረበባቸው ክስ ላይ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እንደተጀመረና እሳቸው በፌስቡክ ገጻቸው ባሠራጩት መጣጥፍ ለማስቀጠል የተደረገ እንደሆነ መገለጹ፣ ከአዋጁ መንፈስ ውጪ መሆኑን በመጠቆም ክሱ ውድቅ ተደርጐ በነፃ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡

አቶ ዮናታን በክስ መቃሚያቸው ላይ እንዳብራሩት፣ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ (4)ን መተላለፋቸው ተገልጿል፡፡ በአንቀጹ እንደተገለጸው ተላልፈዋል የተባለው ድርጊት ማቀድ፣ መዘጋጀት፣ ማሴር፣ ማነሳሳትና መሞከር የሚል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ደግሞ በክሱ ያሰፈረው አቶ ዮናታን ኦነግ ያስጀመረውን አመፅና ብጥብጥ ለማስቀጠል በፌስቡክ ገጻቸው ላይ የተለያዩ ቀስቃሽ ጽሑፎችን ማሠራጨታቸውን የሚገልጽ በመሆኑ፣ በአዋጁ አንቀጽ ሥር ከተመለከቱት ውስጥ በአንዱም የማይሸፈን መሆኑን በመግለጽ አብራርተዋል፡፡ በመሆኑም የዓቃቤ ሕግ ክስ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 112 የተደነገገውን ማለትም ‹‹… ወንጀለኛው የፈጸመው ተግባር፣ ወንጀል ከሚያደርገው የሕግ አነጋገር ጋር በጣም የተቀራረበ መሆን አለበት፤›› ከሚለው ድንጋጌ ጋር የሚጋጭ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አቶ ዮናታን ፈጽመውታል ለተባለው ክስ በማስረጃነት የቀረበው የሰነድ ማስረጃ በፌስቡክ ገጻቸው ተሠራጨ የተባለው መጣጥፍ መሆኑን ገልጸው፣ ፌስቡክ ደግሞ ዘመናዊ የመልዕክት መለዋወጫ ዘዴ መሆኑን፣ ይኼም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 29 ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ድንጋጌ ከመሆኑ አንፃር፣ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በየትኛውም ሕግ ገደብና ክልከላ ያልተደረገባቸውና በቀረበባቸው ክስ በተጠቀሰው አንቀጽ ሥር የማይሸፈንና የሽብርተኝነት ተግባር አለመሆኑንም አቶ ዮናታን አክለዋል፡፡ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ ሕገ መንግሥታዊና ሰብዓዊ መብታቸውን ለማስከበር የተቀመጡ መርሆዎችንና ድንጋጌዎችን የማያሟላ ክስ መሆኑን ገልጸው፣ ተሰርዞ በነፃ እንዲሰናበቱ በተደጋጋሚ ጠይቀዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸው ክስ ሐሳቡና ይዘቱ አርትኦትና የቃላት ማስተካከል የጎደለው ከመሆኑም በተጨማሪ ለመረዳት የሚያስቸግር፣ በረጃጅም ዓረፍተ ነገሮችና አባባሎች አሳሳች ሆኖ የቀረበ በመሆኑ በወንጀል መዝገብ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 111 ድንጋጌን ማለትም፣ ‹‹… የክስ ማመልከቻ ቀን፣ ዓመተ ምሕረት የተጻፈበትና የተፈረመበት…›› የሚለውን የማያሟላ መሆኑን አቶ ዮናታን ጠቁመው፣ ክሱ ተሰርዞ በነፃ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ክሱን የሚያሻሽል ከሆነም በሕጉ አግባብ ሥነ ሥርዓቱን ተከትሎ በሚያቀርበው ክስ ላይ የሚጠቅሰው የሕግ አንቀጽ፣ ከክሱ ጋር የሚቀራረብና የተከሳሹን የመከራከር መብት የማያጣብብ አድርጐ እንዲያዘጋጅ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው፣ ጉዳዩን ለሚከታተለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. አመልክተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም የዓቃቤ ሕግን ምላሽ ለመጠባበቅ ለግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ፎቶና ዜናው የሪፖርተር ነው

በዓል ማክበርም አለማክበርም እኩል መብት የሚሆኑት መቼ ነው?


 

እዚህ ባለሁበት አገር ግንቦት 17 ቀን ታላቅ በአል ነበራቸው። በአሉ በሔራዊ ቀን ነው። ይህ በየዓመቱ የሚክበር በዓል ስብሰባ ውጡ፣ ተሰለፉ፣ ባንዲራ ያዙ፣ ዘምሩ ፣ ጨፍሩ… ብሎ ነገር የለውም። ለማለት ቢሞከርም ሰሚ የለም። በደፈናው ” ብሔራዊ ቀንህን አክብር፣ አክበሪ” የሚል ፕሮፓጋንዳና አይሰማም።  ሙሉ ቤተሰብ በአስር ሺዎች የሚሸጥ ባህላዊ ልብሳቸውን፣ ካልሆነም ሱፋቸውን ለብሰው ሲፈሱ ትንግርት ነው የሚመስለው። የ3 ደቂቃ ንግግር ቢጤ ይደረግና መብላት መጠጣት ነው። መሳሪያ፣ ጦር ሰራዊት፣ ፖሊስ፣ ታንክ ….. ቀርቶ ጥሩ ዱላ የያዘ የጸጥታ ሃይል አይታይም። ይህንን ከአገሬ ጋር ለማወዳደር ፈልጌ ሳይሆን ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ነው።

17maydownload (2)

 ግንቦት20ን አስመልክቶ ብዙ ዓይነት ክርክር ይነሳል። ከሁለቱም በኩል ያለው እሳቤ አንዱ የሌላውን ፍላጎት በማክበር ላይ የተመሰረተ አይደለም። እንደኔ እንደኔ በዓል የሚባል ነገር ማክበር በህግ ቢከለከል እወዳለሁ። በተለይ አሁን አሁን ደግሶ መብላት፣ ለድግስ በጀት መመደብ ለኢትዮጵያ በባዶ ቂጥ የመቀማጠል ያህል ይመስለኛል። ለፌሽታ አላደለንም።
አዲስ ዓመት ብሎ በቄጤማ ጉዝጉዋዝ ከተማ ማቆሸሽ፣ ቱቦ መድፈን ስልጣኔ አይደለም። ወደ ፖእለቲካው ስንመለስ ግንቦት 20ን ማክበር ህልውናቸው የሆነ በደስታ ሲያከብሩ፣ ማክበር አንፈልግም የሚሉም መብታቸው የዛኑ ያህል ሊከበር ይገባል። ከዚህ ውጪ ግን ግንቦት 20 የግድ ” ህልውናህ” ይሁን ብሎ ጫና ማድረግ ቀናነት የጎደለው አስተሳሰብ ይመስለኛል። አንዳንድ አስገዳጅ ደብዳቢዎችን በማህበራዊ ገጾች ላይ ሳነብ ተገረመኩ። አፍቃሪ ኢህአዴጎች ሁሉም በድርጅታቸው ፍቅር እንዲነደፍ መመኘታቸውን ማቆም አለባቸው።  ግንቦት 20ን የሚያከበሩትንም በነገር መጎንተል አግባብ አይሆንም።
ከዚህ ሁሉ ግን ራሱ ኢህአዴግ እንዲህ ያሉ ድግሶችን በልማት ስራና ያለፉ ጥፋቶችን መመልከቻ ሲምፖዚየም በማዘጋጀት እንዲከበር ቢያደርግስ ?
ፎቶ- የተጠቀምኩት ለንጽጽር ሳይሆን ፣ እኛ ገና በባንዲራ እንኩዋን  ስላስተስማምን የቅናት መንፈስ እንደሚያቃጥለኝ ለማሳየት ነው

የአቶ አንዳርጋቸው ልጅ የእንግሊዝን መንግስት ልትከስ ነው


d2116b2c80a820e8b999cf4c7e244f06_XL

በየመን በኢትዮጵያ መንግስት በቁጥጥር ስር የዋሉትና በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጅ የሆነቺው የ9 አመቷ ታዳጊ ምናበ አንዳርጋቸው፤ አባቴ ከእስር የሚፈታበትን መንገድ አላመቻቸም በሚል የእንግሊዝን መንግስት ልትከስ እንደሆነ ዘ ኢንዲፔንደንት ዘገበ፡፡ የታዳጊዋ የህግ ባለሙያዎች የእንግሊዝ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚገባውን ያህል አለመከታተሉና ከእስር የሚፈቱበትን መንገድ ለመፈለግ እስከመጨረሻው አለመግፋቱ በህግ ያስጠይቀዋል ማለታቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ የእንግሊዝን መንግስት በህግ መጠየቁ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከእስር የሚፈቱበትን ሁኔታ ለመፍጠር ያስችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው መናገራቸውን ገልጧል፡፡
በእንግሊዝ የውጭና የኮመንዌልዝ ቢሮ ፤የአቶ አንዳርጋቸው እስርና አያያዝ ተቀባይነት የሌለው ነው ቢልም፣ ከእስር ተፈትተው እንዲወጡ ግፊት አላደረገም ያለው ዘገባው፣ ልጃቸው ምናበ፤ አባቷ የሚፈቱበትን ሁኔታ ለመፍጠር ተጨማሪ ጥረት ያደርጋል በሚል ተስፋ መንግስትን ለመክሰስ መዘጋጀቷን ጠቁሟል፡፡source ADDIS ADMAS